የልጅነት ማዕከል

2013 የተመሰርተው ማዕከላችን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ‘22 ማዞሪያአካባቢ ይገኛል። ማእከሉ የተገነባው ከፍራሽ ቤቶች በተሰበሰቡ ቁሶች እና አገልሎት አይሰጡም በተባሉ እቃዎች መልሶ እና አሻሽሎ በመጠቀም ነው፡፡ በርካታ ሃገር በቀል እፅዋቶች እና Herbal and Medicinal plants የመኣከሉ ድምቀት ናቸው፡፡

በማዕከላችን የሽመና እና የጥጥ ፈተላ ስፍራ የስዕል እና የእደጥበብ ስፍራ በወዳደቁ እና በተጣሉ ነገሮች መልሶ እና አሻሽሎ የመስራት ስፍራ የጭቃ ማቡካት እና የሸክላ ስራ ስፍራ የባህላዊ ዳቦዎች ማስጋገሪያ ጥግ እና የልጅነት ጨዋታዎችን እና ተፈጥሮአዊ መዝናኛዎችን እንዲሁም የዶሮዎች መመገቢያ እና የዕፅዋት ማዕከል የያዘ ነው ፡፡

ለተስተካከለና ለጤናማ እድገት የሚረዱ ሀገር በቀል የሆኑ ጥራጥሬዎች እና እሕሎችን በመጠቀም በራሳችን ፈጠራ የሚዘጋጁ ጤናማና ቀላል Vegetarian ምግቦች እና ጣፋጮችን በሀገራዊ ሙያ ከሽኖ የሚያቀርብ ምግብ ቤት በማዕከሉ ይገኛል።

በተጨማሪም ማዕከሉ የባዛር ፣ ኤግዝቢሽን የልደት እና ወርክ ሾፕ የመሳሰሉ ዝግጅቶችን ያስተናግዳል።

The Nu Chika Enabuka Family Center is a children’s play area with adult supervision that provides a variety of parent-child activities focused on the physical, emotional, and social growth of kids. A sizable, full-scale play structure is available for the children, while a smaller one is available for toddlers. In addition, we sell unique toys, and other goods, as well as provide consumers with nutritious snacks, drinks, and desserts. The facilities are made to keep kids active, amuse them, and stimulate them while fostering strong cultural and social skills.