በጥቅምት 6 2014 ዓም በውቡ መስቀል አደባባይ የተደረገው ኑ ጭቃ እናቡካ ከኦሞ ጋር ልዩ የቤተሰብ ፌስቲቫል 10,000 የሚደርሱ ታዳሚዎች የታደሙበት ልጆች ከወላጆቻቸው ጋር ጭቃ ያቦኩበት የልጅነት ጨዋታዎች የተጫወቱበት እና የተማሩበት ፣የሙዚቃ ትርኢቶች ከውዝዋዜ እና አስደናቂ የሰርከስ ትርኢቶች የታዩበት ወላጆች ለልጆቻቸው የልጅነት ጨዋታቸውን ያሳዩበት የቁምነገር እና የደስታ ቀን ሆኖ አልፏል በእለቱ በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ለማስመዝገብ የተሞከረ በብዙ ተሳታፊዎች የተሰራ 51 ሜትር የረዘመ በዓለም ረጅሙ አባ ጨጓሬ ተሰርቷል